am_tn/act/23/31.md

739 B

የሐዋርያት ሥራ 23፡ 31-33

ስለዚህም ወታደሮቹ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ በዚህ ሥፍራ ላይ “ስለዚህ” የሚለው ቃል ከዚህ በፊት በተነገረ አንድ ነገር ምክንያት ይህ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የወታደሮቹ አለቃ ለወታደሮቹ የሰጣቸው ትዕዛዝ ጳውሎስን እንዲጠብቁት ነው፡፡ አንቲጳጥሪስ ይህች ሄሮዶስ ለአባቱ አንቶጳጥሪ ክብር ሲል የገነባት ከተማ ናት፡፡ በዘመናችን እስራኤል ውስጥ ትገኛለች፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/translate-names)