am_tn/act/21/37.md

1.9 KiB

የሐዋርያት ሥራ 21፡ 37-38

ጳውሎስ ሊቀርብ ሲል አማራጭ ትርጉም: "ወታደሮቹ ጳውሎስን ለማቅረብ ዝግጅታቸው ስያጠናቅቁ" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]]) የወታደሮች ካምፕ ይህንን በ ACT 21:34 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ ዋናው አለቃ የወታደሮች አለቃ ወይም የስድስት መቶ ወታደሮች አለቃ የግሪክ ቋንቋ ትናገራለህን? አንተ በእኛ ላይ አምጾ አራት ሺህ አሸባሪዎችን ይዞ ወደ በረሃው የገባው ግብጻዊው ሰው አይደለህምን? የወታደሮች አለቃ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው ጳውሎስ ነው ብሎ ያሰበው ሰው አለመሆኑን በተረዳ ጊዜ መገረሙን ለመግለጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "የግሪክ ቋንቋ መናገር ትችላለህ እንዲያውም አራት ሺህ አሸባሪዎችን ይዞ ወደ በረሃ የገባው ሰው ነህ፡፡" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-rquestion]]) አንተ ግብጻዊው ሰው አይደለህምን ጳውሎስ ወደዚያ አከባቢ ከመሄዱ ጥቂት ጊዜ በፊት ከግብጽ ምድር የመጣ አንድ ስሙ የማይታወቅ ሰው በኢየሩሰሌም ውስጥ በሮማዊያን ላይ ሰዎች እንዲያምጹ አድርጓል፡፡ ከዚያም “ወደ ምድረበዳ አምልጦ ሄዷል”፡፡ ስለዚህም ይህ የወታደሮች አለቃ ጳውሎስ ይህ ሰው ይሆን እንደሆነ አስቧል፡፡ አራት ሺህ አሸባሪዎችን "ከእነርሱ ጋር የማይስማሙ ሰዎችን ሁሉ የሚገድሉ አራት ሺህ ወንዶች" (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/translate-numbers)