am_tn/act/16/11.md

966 B

የሐዋርያት ሥራ 16፡ 11-13

አጠቃላይ መረጃ: ቁጥር 13 ሊዲያ የተባለችው ሴት ታሪክ የሚጀምርበት ነው፡፡ ይህ አጭር ታሪክ በጳውሎስ ጉዞ ውስጥ የተከናወነ ነው፡፡ አደረገን በዚህ ሥፍራ ላይ "እኛ" የሚለው ቃል ሁሉን የሚያቅፍ ሆኖ ጳውውሎስን እንዲሁም የሐዋርያት መጽሐፍ ጸሐፊ የሆነውን ሉቃስን የሚያካትት ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-inclusive]]) ሳሞትራቄ . . . ናጱሌ እነዚህ በፊልጵስዮስ አቅራቢያ የሚገኙ ከተሞች ናቸው፡፡ (ተመልከት [[rc:///ta/man/translate/translate-names]]) የሮም ግዛቶች ሮማዊያን በጦርነት አሸንፈው በዚያን ጊዜ የያዝዋቸው ሥፍራዎች ሲሆኑ በተለይም ወታደሮች የሠፈሩባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡