am_tn/act/10/30.md

1.8 KiB

የሐዋርያት ሥራ 10፡ 30-33

የሐዋርያት ሥራ 10፡ 30-33 አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ቆርኖሊዎስ ለጴጥሮስ ጥያቄ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፡፡ አጠቃላይ መረጃ: በቁጥር 31 እና 32 ላይ ቆርኖሊዎስ መልአኩ በዘጠኝ ሰዓት በተገለጠለት ጊዜ የተናገረውን ነገር ቃል በቃል በመጥቀስ ምላሽ ሰጠ፡፡ ከአራት ቀናት በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል መሠረት ይህ የነበሩበትን ቀንንም ያካትታል፡፡ በዘመናችን የምዕራባዊያን ባሕል መሰረት ይህ እንዲህ ሊሆን ይችላል “ከሦስት ቀናት በፊት” እየጸለይኩ ሳለ አንዳንድ ጥንታዊያን ቅጂዎች “ከእየጾምኩ” ይልቅ “እየጾምኩና እየጸለይኩ ሳለ”S ይላሉ፡፡ በዘጠን ሰዓት ላይ አይሁዊያን ወደ እግዚአብሔር የሚጸልዩበት የከሰዓቱ የተለመደው ሰዓት፡፡ እግዚብሔር አስቦሃል "እግዛብሔር ተመልክቶሃል" ስምኦን እንዲሁም በሌላ ስሙ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራ ሰውን አስጠራ "ጴጥሮስ ተብሎ የሚታወቀውን ስምኦንን አስጠራ" እኔ ወደ አንተ እልከዋለሁ "እርሱን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጴጥሮስን ብቻ ነው፡፤ እኛ ሁላችን በዚህ አለን "እኛ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጴጥሮስ ስናገር ይሰሙ ዘንድ ወደቆርኖሊዎስ ቤት የተጠሩትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡ “እኛ” የሚለው ቃል ጴጥሮስን አያካትትም፡፡ (ተመልከት፡ rc://*/ta/man/translate/figs-exclusive)