am_tn/act/10/27.md

1.3 KiB

የሐዋርያት ሥራ 10፡ 27-29

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጴጥሮስ በቆርኖሊዎስ ቤት ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲህ ሲል ንግግር አደረገ፡፡ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ "ቆርኖሊዎስን አናገረው" ብዙ ሰዎች ተሰብስበው አገኘ "ብዙ አሕዛብ በዚያ ተሰብስቦ አገኘ፡፡" ከዚህ በተዘዋዋሪ መንገድ መረዳት የሚቻለው ቆርኖሊዎስ የጋበዛቸው ሰዎች አሕዛብ መሆናቸውን ነው፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-explicit) ለአይሁዳዊ ሰው ይህ በሕግ የተፈቀደ አይደለም "ይህ ለአይሁዳዊ ሰው በሕግ የተከለከለ ነው" ይህንን አንተ ራስህ ታውቃለህ ጴጥሮስ ለቆርኖሊዎስ እና እርሱ ለጋበዛቸው እንግዶች በመናገር ላይ ነው፡፡ “ስለዚህ ለምን እንደ አስጠራኸኝ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡” ምንም እንኳ ቆርኖሊዎስ ጥያቄውን ያቀረበው በቀጥታ ለቆርኖሊዎስ ቢሆንም “እናንተ” የሚለው ቃል በዚያ ሥፍራ ያሉትን አሕዛቦችን ሁሉ ያካትታል (ብዙ ቁጥር ነው)፡፡