am_tn/act/07/01.md

1.0 KiB

የሐዋርያት ሥራ 7፡ 1-3

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: በ ACT 6:8 ላይ የተጀመረው ስለእስጥፋኖስ የተነገረው ታሪክ ይቀጥላል፡፡ አጠቃላይ መረጃ: በቁጥር 2 ላይ እስጥፋኖስ ለሊቀ ካህኑ እና ሸንጎው ምላሽ መስጠቱን ይጀምራል፡፡ ንግግሩንም የጀመረው በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ስለተፈጸሙ ነገሮች በመናገር ነው፡፡ ወንድሞች እና አባቶች አድምጡኝ እስጥፋኖስ ንግግሩን የጀመረው ለእነርሱ አክብሮት እንዳለው በሚያሳይ መልኩ እንደዘመዶቹ ሰላምታ በማቅረብ ነው፡፡ አባታችን እስጥፋኖስ አድማጮቹን “አባታችን አብረሃም” በሚለው ንግግሩ ውስጥ አካቷቸዋል፡፡ ምድርህንና ዘመዶችህን ተው "የአንተን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብረሃምን ነው (ነጠላ ቁጥር)፡፡