am_tn/act/01/01.md

1.7 KiB

የሐዋርያት ሥራ 1፡ 1-3

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ሉቃስ ለቴዎፍሎስ ይህንን መጽሐፍ መጻፍ ለምን እንዳስፈለገው ያብራራል፡፡ ከዚህ መጽሐፍ በፊት በጻፈው መጽሐፉ ከዚህ መጽሐፍ በፊት የጻፈው መጽሐፍ የሉቃስ ወንጌልን ነው፡፡ ቴፍሎስ ሉቃስ ይህንን መጽሐፍ የጻፈው ቴዎፍሎስ ተብሎ ለሚጠራ ሰው ነው፡፡ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በባሕላቸው ደብዳቤ በሚጻፍበት ወቅት መግቢያው ላይ የሚጻፈውን ነገር በመከተል “ውድ ቴዎፍሎስ ሆሕ” በማለት ተርጉመውታል፡፡ ቴዎፍሎስ ማለት “የእግዚአብሔር ወዳጅ” ማለት ነው፡፡(ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/translate-names) እስከ አረገበት ቀን ድረስ ያለውን ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ያረገበት ወቅት ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሰጠውን ትዕዛዝ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በተወሰኑ ነገሮች ዙሪያ የተለያዩ መመሪያዎችን በመስጠት ሂደት ውስጥ መሪቶታል፡፡ ከመከራው በኋላ ይህ ኢየሱስ የተቀበለውን መከራን እና በመስቀል ላይ የሞተውን ሞት ያመለክታል፡፡ ሕያው ሆኖ እንደገና ለእነርሱ ታያቸው ኢየሱስ ከመጀመሪያዎቹ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት በተጨማሪ ለብዙ ሰዎች ከሞት ከተነሣ በኋላ ታይቷቸዋል፡፡