am_tn/2ti/04/06.md

2.3 KiB

2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡ 6-8

ከአንተ የሚለይበት ጊዜ ተቃርቧል "በቅርቡ እሞታለሁ፣ ይህችንም ምድር ትቼ እሄዳለሁ" (UDB)፡፡ ጳውሎስ ከእንግዲህ በኋላ ለረጅም ጊዜ እንደማይኖረ አውቆዋል፡፡ ሩጫዬን በተገቢው ሁኔታ አጠናቅያለሁ ይህ የድብድብ፣ የትግል ወይም የቡጥ እስፖርታዊ ምሳሌ ነው፡፡ ጳውሎስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ ይህ “የሚችለውን ሁሉ ጥረት አድርጌያለሁ” ወይም “ያቅሜን ያህለ አድርጌያለሁ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡(ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) ሩጫዬን ጨርሻለሁ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር የሚያሳየው በሩጫ ውድድር ላይ የመጨረሻ መስመር ላይ መድረስን ከሕይወት ፍጻሜ ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “ማድረግ የሚገባኝነት ነገር ጨርሼያለሁ፡፡(ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) እምነትን ጠብቄያለሁ አማራጭ ትርጉሞች 1) "የሚናምነውን ነገር ከስህተት ጠብቄያለሁ" ወይም 2) "አገልግሎቴን በታማኝነት ጨርሼያለሁ" (UDB). የጽድቅ አክልል ለእኔ ተቀምጦልኛል አማራጭ ትርጉም: "የትድቅ አክልል ይሰጣኛል" የጽድቅ አክሊል አማራጭ ትርጉሞች 1) አክሊል እግዚአብሔር በትክክለኛ መንገድ ለኖሩ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ነው፡፡ (UDB) ወይም 2) አክሊል ለጽድቅ ምሳሌ ነው፡፡ የውድድር ዳኛው ለአሸናፊው አክሊል እንደሚሰጠው ሁሉ ጳውሎስ ሕይወቱን አጠናቆ ሲሄድ እግዚአብሔር ጳውሎስን ጸድቅ ብሎ ይጠራዋል፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) አክሊል የሩጫ ውድድርን አሸንፈው ለሚገቡ ሮሯጮች የሚሰጥ ከወይራ ቅጠል የሚሠራ አክሊል ነው፡፡ በዚያ ቀን "ጌታ ዳግም በሚመጣት ቀን" ወይም "እግዚአብሔር ሕዝቡ ላይ በሚፈርድበት ቀን"