am_tn/2ti/04/03.md

1.9 KiB

2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡ 3-5

ጊዜ ይመጣልና "ለወደፊት . . . ጊዜ ይመጣልና" ሰዎች አውዱ እንደሚያሳየው እነዚህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ናቸው (UDB)፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ይህ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ እና ትክክለኛ ብላ የሚትቀበለው ማለት ነው፡፡ ከእነርሱ ፍላጎት ጋር ተስማሚ የሆነ ትምህርትን ከሚያስተምህሩ መምህራን ጋር ይሆናሉ፡፡ በዚህ መልኩ ጆራቸውን ያኩላቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉሞች 1) ከግል ፍላጎታቸው የተነሣ ለመስማት የሚፈልጉትን ነገር በሚነግሯቸው መምህራን ዙሪያ ይሰበሰባሉ፡፡ ወይም 2) ከእነርሱ የግል ፍላጎት ጋር ከሚስማሙ መምህራን ዙሪያ ይሰበሰባሉ እነርሱም የሚፈልጉትን በጆሮዋቸው ይነግሯቸዋል፡፡ ለራሳቸው መሻት "የግል ፍላጎታው" ጆሮዋቸውን ያኩላቸዋል "እነዚህ መምህራን ጆሮዋቸውን ያኩላቸዋል፡፡" "ጆሮዋቸውን ማከክ" ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን የሚያሳየው መስማት የሚያስደስታቸውን ፣ ደስተኞች እንደሆኑ የሚያደርጋቸውን ነገር መናገር ማለት ነው፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) የወንጌላዊነት ሥራ ይህ ማለት ኢየሱስ ማን እንደሆነ፣ ለእነርሱ ምን እንዳደረግ እና ለእርሱ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለሰዎች መናገር ማለት ነው፡፡ አገልግሎት ስለ እግዚአብሔር እነርሱን በማስተማር እነርሱን በመንሳዊ ነገር ማገልገል ማለት ነው፡፡