am_tn/2ti/02/16.md

1.8 KiB

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡ 16-18

ቃሉ ልክ እንደ ጋንግሪን ይሠራጫል "የሚናገሩት ነገር ልክ እንደ በሽታ ይሰራጫል፡፡" ጋንግሪን በሰው ሰውነት ውስጥ በፍጥነት እንደሚሰራጭ እና አካሉን እንደሚያጠፋ ሁሉ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት ነገር ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ በመሰራጨት የሰሙትን ሰዎች እምነት ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ቃላቸው በፍጥነት ይሰራጫል እንዲሁም ልክ እንደ ጋንግሪን ከፍተኛ ጉዳት ያሳድራል" ወይም "የሚሉትን ነገር ሰዎች በፍጥነት ይሰሙታል እንዲሁም በዚህ ንግግር ይጎዳሉ፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-simile) ጋንግሪን የሞተ፣ የበሰበበሰ ሥጋ፡፡ ጋንግሪን በሰውነት ውስጥ እንዳይሰራጭ እና ሰውዬውን እዳይገድለው ማድረጊያ ብቸኛው መንገድ የተበከለውን የሰውነት ክፍል ቆርጦ መጣል ነው፡፡ ከእውነት ርቀዋል ይህ እነዚህን ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላል 1) "ስለ እውነት ተሳስተዋል" ወይም "ስለ እውነት በስህተት ውስጥ ናቸው፣" ዒላዋን እንደ ሳተ ቀስት ወይም 2) "በእውነት ማመን አቁመዋል፡፡" ትንሳዔ ...ሆኗልd "እግዚአብሔር የሞቱ አማኞችን ወደ ዘላለማዊ ሕይወተ አስነስቷቸዋል" የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ "የአንዳንድ አማኞቸን እምነት ጥርጣሬ ውስጥ ይጥላሉ" ወይም "አንዳንድ አማኞች ማመናቸውን እንዲያቆሙ በማሳመን"