am_tn/2ti/01/06.md

2.4 KiB

2ኛ ጢሞቲዎስ 1፡ 6-7

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጳውሎስ ጢሞቴዎስ በኃይል፣ በፍቅር እና በደቀ መዝሙርነት እንዲኖር ያበረታታዋል፡፡ በተጨማሪም በጳውሎስ መታሠር እንዳያፍር ምክንያቱም የጳውሎስ መከራ በክርስቶስ በማመኑ ምክንያት ነው፡፡ ይህ ምክንያት ነው "በዚህ ምክንያት" ወይም "በኢየሱስ ላይ ባለህ እውነተና እምነት የተነሣ" ወይም "በኢየሱስ ላይ እውነተኛ እምነት ስላለህ" አስታውስሃለሁ "እኔ አስታውስሃለሁ" ወይም "እንደገና እነግርሃለሁ" እጅ በመጫን በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚብሔር ስጦታ አነሳሳለሁ ጳውሎስ በጢሞቴዎስ ላይ እጆቹን በመጫን በእርሱ ላይ ያለውን መንፈስ ቅዱስ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን አረጋግጧል፡፡ ጳውሎስ እየነገረው ያለው ነገር ለክርስቶስ በሚሠራበት ወቅት እነዚህን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች “እንደገና እንቀሰቅስ” ወይም “እንዲያነቃቃ” ነው፡፡ የከሰል እሳትን ማራገብ ወይም ማቀጣጠል የሚለው ምስላዊ ገለጻ በጢሞቴዎስ የተዘነጉ ወይም በጢሞቴዎስ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያልሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎቸን መቀስቀስን ያመለክታሉ፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) ለእግዚአብሔር "በእግዚአብሔር ምክንያት" እግዚአብሔር የፍርሃትን መንፈስ አልሰጠንም ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ዘንድ መንፈስን ተቀብሏል፡፡ በጢሞቴዎስ ላይ እጆቹን በሚጭንበት ጊዜ በጢሞቴዎስ ላይ ተመሳሳይ መንፈስ ያርፍበታል፡፡ ይህ መንፈስ ደግሞ እግዚአብሔር ወይም ሌሎች ሰዎችን እንዲፈራ አያደርገውም፡፡ ራስን የመግዛት መንፈስ አማራጭ ተትርጉሞች “የእግዚአብሔር መንፈስ ራሳችን የመግዛት መንፈስን ይሰጠናል" (UDB) ወይም 2) "የእግዚአብሔር መንፈስ በተሳሳተ መንገድ የሚሄዱ ሰዎችን እንድናስተካክል ያደርገናል፡፡"