am_tn/2ti/01/01.md

2.1 KiB

2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡ 1-2

ጳውሎስ "ከጳውስ" ወይም "እኔ ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ ጻፍኩላችሁ" በእግዚአብሔር ፈቃድ አማካኝነት "ከእግዚብሔር ፈቃድ የተነሣ" ወይም "እግዚአብሔር ይህንን ነገር በመፈለጉ ምክንያት፡፡" ጳውሎስ ሐዋርያ የሆነው እግዚአብሔር ጳውሎስ ሐዋርያ እንዲሆን በመፈለጉ እንጂ ሰዎች ሐዋርያ እንዲሆ ስለመረጡት አይደለም፡፡ እንደ አማራጭ ትርጉሞች፡ 1) "ከ ጋር በመስማማት" ትርጉሙም እግዚአብሐየር ለኢየሱስ በገባው ቃለል መሠረት ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል እንዲሁም ጳውሎስን ሐዋርያ አድርጓል ወይም 2) "ለዚህ ዓላማ ሲባል፣" ትርጉሙም እግዚአብሔር ጳውሎስን የሾመበጽ ምክንያት ጳውሎስ በኢየሱስ በኩል የሚገኘውን ሕይወት ለሌሎች ሰዎች ይናገር ዘንድ ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ የሚገኘውን የሕይወት ተስፋ "በክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑ ሰዎች ሕያዋን እንደሚሆኑ እግዚአብሔር የተስፋ ቃልን ሰጥቷል፡፡" የተወድህ ልጄ ሆይ "ውድ ልጄ ሆይ" ወይም "የተወደድከው ልጄ ሆይ" ወይም "የሚወድህ ልጄ ሆይ፡፡" ጢሞቴዎስ ወደ ክርስቶስ የመጣው በጳውሎስ አማካኝነት ነው ስለዚህም ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ልክ እንደ ገዛ ልጁ አድርጎ ይመለከተው ነበር፡፡ ጸጋ፣ ምህረት እና ሰላም ከ . . . "ጸጋ፣ ምህረት እና ሰላም ለእናነት ከ . . . ዘንድ ይሁንላችሁ" ወይም "ከውስጥ መልካምነትን፣ ምህረትን እና ሰላምን ከ . . . ዘንድ ይሁንላችሁ" እግዚአብሔር አባት "አባታችን የሆነው እግዚአብሔር" እናም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ "እንዲሁም ጌታችን ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ዘንድ"