am_tn/2sa/24/15.md

1.9 KiB

የተወሰነ ጊዜ

ይህ እግዚአብሔር መቅሰፍቱን ለማቆም የወሰነበት ጊዜ ነው፡፡

ሰባ ሺህ

"70,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ከዳን እስከ ቤርሳቤህ

እዚህ ስፍራ በሰሜን ጫፍ የሚገኘው ዳን እና በደቡብ ጫፍ የሚገኘውን በርሳቤ መጠቀሱ መላው የእስራኤል አገር መጠቀሱ ነው፡፡ (ጽንፎች የሚለውን ይመልከቱ)

መልአኩ ኢየሩሳሌምን ሊያጠፋት እጆቹን ዘርግቶ ደረሰ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የመልአኩን ሀይል ለመግለጽ የዋለ ነው፡፡ "መልአኩ በኢየሩሳሌ የሚኖሩ ሰዎችን ሊያጠፋ ተቃርቦ ነበር" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ ከደረሰው ጥፋት የተነሳ ምህረት አደረገ

ይህ ማለት ያህዌ መልአኩ ሊያደርስ ያለውን ክፉ ነገር አስቆመ፡፡ "ያህዌ ስለ ደረሰው ጥፋት አዘነ"

እጅህን መልስ

"እጅ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚገልጸው የመልአኩን ሀይል ነው፡፡ "ከዚህ በላይ ጉዳት አታድርስባቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ኦርና

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ዐውድማ

ዐውድማ ፍሬውን ከገለባ ለመለየት የተዘጋጀ ለጥ ያለ ወለል