am_tn/2sa/23/13.md

1.2 KiB

ከሰላሳዎቹ ውስጥ ሶስቱ

እነዚህ በ 2ሳሙኤል 23፡8-12 ውስጥ የተጠቀሱት እንዚያው ሶስቱ ወታደሮች አይደሉም

ሰላሳዎቹ

"30ዎቹ" ወይም "ሰላሳዎቹ የእስራኤል ጀግና ወታደሮች፡፡" የዚህ ሀሳብ ሙሉ ትርጉም ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ (ቁጥሮች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የዓዶላም ዋሻ

"ዓዶላም ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ዋሻ፡፡" ዓዶላም የሚገኘው ቤተልሔም አጠገብ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የራፋይም ሸለቆ

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ ይህ በ2 ሳሙኤል 5፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በጠንካራ ይዞታው/በምሽጉ

"በተጠበቀ ቦታው"

ፍልስጥኤማውያን በቤተልሔም ይገኙ ነበር

"ጥቂት ፍልስጥኤማውያን ወታደሮች የቤተልሔምን መንደር ተቆጣጥረው ነበር"