am_tn/2sa/23/05.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ቀጣይ የዳዊት ማጠቃለያ ቃል ነው፡፡

በውኑ የእኔ ቤት በያህዌ ፊት እንደዚህ አይደለምን?

እዚህ ስፍራ ላይ ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር መስማማቱን ይናገራል፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የእኔ ቤት በውኑ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሁ አይደለምን!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ… መንገድ አላበጀምን?

ዳዊት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ እውቅና ይሰጣል፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱ በእርግጥ… መንገድ ያበጃል፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ስርአት ያለው እና እርግጠኛ

ይህ ማለት የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በዳዊት ቤት የታመነ፣ በሚገባ የተቀናጀ እና የማይለወጥ ነው፡፡

እርሱ ደህንነቴን፣ መሻቴን… ፍጹም አላደረገምን?

ዳዊት ሁልጊዜም እግዚአብሔር እንደሚረዳው እና እንደሚያበለጽገው ያምናል፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱ ደህንነቴን ፍጹም ያደርጋል ደግሞም መሻቴን ሁሉ ይሰጠኛል፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)