am_tn/2sa/23/03.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ቀጣይ የዳዊት ማጠቃለያ ቃል ነው፡፡

የእስራኤል አምላክ፣ የእስራኤል አለት፣ ይናገራል… እኔ

እዚህ ስፍራ "የእስራኤል አምላክ" የሚለው "የእስራኤል አለት" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለቱ ሀረጋት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻሉ፡፡ ዳዊት እግዚአብሔርን ከአለት ጋር የሚያነጻጽረው እርሱ ህዝቡን ለመጠበቅ ያለውን ሀይል ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን በመፍራት የሚመራ፣ በሰዎች ላይ በጽድቅ የሚገዛ

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ንጉሡ እግዚአብሔርን እንደሚያከብር እና እግዚአብሔር እርሱ እንዲያደርግ የሚፈልገውን እንደሚያደርግ ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ፍርሃት /እግዚአብሔርን በመፍራት

"እግዚአብሔርን መፍራት/ማክበር"

እርሱ እንደ ማለዳ ብርሃን ይሆናል… ከዝናብ በኋላ እንደሚወጣ ፀሐይ

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ንጉሡን ከማለዳ ብርሃን እና ከዝናብ በኋላ ከሚወጣ ዝናብ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ እነዚህ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እና ለህዝቡ መባረክ ምክንያት መሆኑን የሚገልጹ መንገዶች ናቸው፡፡ "እርሱ ለሁሉም ደስታ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤያዊ የሚሉትን ይመልከቱ)