am_tn/2sa/23/01.md

1.6 KiB

አሁን

ይህ የመጽሐፉን አዲስ ክፍል ጅማሬ ያሳያል፡፡

እነዚህ የመጨረሻ ቃላት ናቸው

ይህ የሚያመለክተው ዳዊት በ2 ሳሙኤል 23፡2-7 የሚናገረውን ነው፡፡

እጅግ የተከበረው ሰው፣ በያቆብ አምላክ የተቀባው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የያዕቆብ አምላክ እጅግ ያከበረው እና የቀባው ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በያዕቆብ አምላክ የተቀባው

መቀባት የሚካሄደው በሰውየው ራስ ላይ ዘይት በማፍሰስ ነበር፡፡ ይህ ይደረግ የነበረው እንደ ንጉሥ ወይም ካህን ሆኖ እግዚአብሔርን የሚያገለግልን ሰው ለመምረጥ ነበር፡፡ (ተምሳሌታዊ/ምልክታዊ ድርጊታዊ የሚለውን ይመልከቱ)

መዝሙረኛው

ይህ መዝሙረ ዳዊትን ወይም መዝሙሮችን የጻፈው ሰው ነው፡፡

በእኔ

በዳዊት

የእርሱ ቃል አንደበቴ ላይ ነበር

እዚህ ስፍራ "በአንደበቴ ላይ" የሚለው ለዳዊት ንግግር ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እርሱ የምናገረውን መልዕክት ሰጠኝ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)