am_tn/2sa/22/47.md

1.2 KiB

አለቴ የተመሰገነ ይሁን፡፡ አምላኬ ከፍ ይበል

እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው የዋሉትም ትኩረት ለመስጠት/ለማጉላት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሁሉም ሰው አለቴን ያወድሰው/ያመስግነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ያድርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእኔ አለት…አለቱ

ዳዊት ያህዌን ከአለት ጋር የሚያነጻጽረው ህዝቡን ለመጠበቅ ያለውን ሀይል ለማጉላት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህዝብን ከስሬ የሚያስገዛልኝ

"ባዕድ ህዝብን ከበታቼ የሚያስገዛልኝ"

ከተነሱብኝ በላይ ከፍ ከፍ አደረግከኝ

"ከጠላቶቼ አዳንከኝ ክብርንም ሰጠኸኝ"

ከአመጸኞች ሰዎች

"ሊጎዱኝ ከሚፈልጉ"