am_tn/2sa/22/40.md

1003 B

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡

ለጦርነት እንደሚታጠቁት ቀበቶ በላዬ ጥንካሬን አደረግህ

እዚህ ሰፍራ ያህዌ የሰጠው ጥንካሬ የተነጻጸረው ዳዊት ታላላቅ ነገሮችን እንዲያደርግ ከሚረዳው የጦር ሜዳ ቀበቶ ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በላዬ የሚነሱብኝን ከበታቼ ጣልካቸው

"ተቃውመው የሚዋጉኝን እንዳሸንፋቸው ረዳኸኝ"

የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ዳዊት ጠላቶቹ ሲሸሹ ጀርባቸውን ይመለከት ነበር ወይም 2) ዳዊት ጠላቶቹን ካሸነፈ በኋላ እግሮቹን በጠላቶቹ አንገት ላይ ያደርግ ነበር

ድምጥማጣቸውን አጠፋኋቸው

"ሙሉ ለሙሉ አጠፋኋቸው"