am_tn/2sa/22/34.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡

እግሮቼን እንደ አጋዘን ፈጣን አድረጓቸዋል፤ ደግሞም እኔን በኮረብቶች ከፍታ ላይ አቁሞኛል

እዚህ ስፍራ የዳዊት እግሮች ግነትን በመጠቀም ከአጋዘን ጋር ተነጻጽረዋል፡፡ ያህዌ ለዳዊት በፍጥነት የመንቀሳቀስ ጥንካሬን፤ ደግሞም ለጥበቃ እና እረፍት አስተማማኝ ስፍራን ሰጥቶታል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ኩሸት እንዲሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

የእኔ እጆች…እና የእኔ እግሮች

እነዚህ ሁለቱም ዳዊትን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ (ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የነሐስ ቀስትን ለማጠፍ

ከብረት የተሰራ ቀስትን መጠቀም የሚችለው በጣም ጠንካራ ሰው ብቻ ነው፡፡