am_tn/2sa/22/32.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡

ከያህዌ በቀር አምላክ ማን ነው፣ ደግሞስ ከአምላካችን በቀር አለት ማን ነው?

ዳዊት ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ከያህዌ በስተቀር አምላክ እንደሌለ አጉልቶ ለመናገር ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ያህዌ ብቻውን አምላክ ነው፡፡ የእኛ አምላክ ብቻ አለት ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አለት ማን ነው

ዳዊት የያህዌን ጥንካሬ እና ህዝቡን ለመጠበቅ ያለውን ችሎታ ለማጉለት ከአለት ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ነውር የሌለበተን ሰው በመንገዱ ይመራዋል

ያህዌ ነውር የሌለበትን ሰው በደህንነት ይጠብቀዋል ደግሞም እርሱን ሊጎዳ የሚችለውን ማናቸውንም ነገር ከመንገዱ ያስወግድለታል፡፡