am_tn/2sa/22/30.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡

በቅጥሩ ላይ መሮጥ እችላለሁ

እዚህ ስፍራ "ቅጥር" የሚለው የድንጋይ ቅጥርን ወይም አንድን የተወሰነ ወታደራዊ ቡድን/ጭፍራን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ይህ ማለት በየትኛውም መንገድ ቢሆን እግዚአብሔር ዳዊት ጠላቶቹን እንዲያሸንፍ ረድቶታል ማለት ነው፡፡

ቅጥርን እዘላለሁ

ዳዊት የያህዌን እርዳታ አጉልቶ እየተናገረ ነው፡፡ "ከተማቸውን የከበበውን ቅጥር መውጣት እችላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል ንጹህ ነው

"ያህዌ የሚናገረው ሁሉ እውነት ነው"

እርሱ ጋሻ ነው

"ጋሻ" የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር የእግዚአብሔርን ህዝቡን የመጠበቅ ሀይል ያጎላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)