am_tn/2sa/22/19.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በመከራዬ/ጭንቀቴ ቀን ሊቃወሙኝ በእኔ ላይ ተነሱ

"ጠላቶቼ በትልቅ ችግር በሆንኩበት ጊዜ በተቃውሞ ተነሱብኝ"

በመከራዬ ቀን

"በመከራዬ ጊዜ"

ነገር ግን ያህዌ ደጋፊዬ ነበር

"ነገር ግን ያህዌ ደገፈኝ" ወይም "ነገር ግን ያህዌ እኔን እረዳኝ"

ሰፊ ስፍራ

ይህ የሚያመለክተው አደጋ የሌለበትን እና ጠላቶቹ እርሱን ሊያጠምዱ የማይችሉበተን ስፍራ ነው፡፡

በእጆቼ ንጽህና መጠን

እዚህ ስፍራ "የእጆቼ ንጽህና" ማለት "ጽድቅ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ "ትዕዛዛቱን ጠብቄአለሁና" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋጋር እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)