am_tn/2sa/22/17.md

743 B

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከብዙ ውሃ አወጣኝ

ዳዊት ጠላቶቹን ሊያሰጥመው ከሚያስፈራራው የውሃ ሙላት ጋር ያነጻጽራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ

የዳዊት ጠላቶች ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነበሩ፡፡ ከጠላቶቹ ሁሉ ስላዳነው እግዚአብሔርን ያመሰግናል፡፡