am_tn/2sa/22/16.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበውን መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም የባህር መንገዶች ታዩ… የአፍንጫው እስትንፋስ

ያህዌ በዳዊት ጠላቶች ላይ ሊቀጣ መነሳቱ የተነጻጸረው በውቅያኖስ ጥልቅ ክፍል እና በመሬት ላይ ነውጥ ከሚፈጥረው ሀይሉ ጋር ነው፡፡ ይህ የእርሱን ታላቅ ሀይል እና ብርቱ ቁጣ ያሳይል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የባህር መንገዶች ተገለጡ/ታዩ

ይህ ማለት የባህር ውሃ ስፍራቸውን ለቀው የውቅያኖስ ወለል ተገለጠ ማለት ነው፡፡

መሰረቶች… ተራቆቱ

ዳዊት የያህዌን ቁጣ ከከምድር መናወጥ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የያህዌ ዘለፋ የምድርን መሰረቶች ገለጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)