am_tn/2sa/22/13.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከፊቱ ከወጣው መብረቅ … መብረቅ ወጣ አጠፋቸውም

ዳዊት ከጠላቶቹ ሊያድነው የመጣውን፣ ከአውሎ ነፋስ ጋር የሚያነጻጽረውን ያህዌን መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ በዳዊት ጠላቶች ላይ የእግዚአብሔርን ሀይል እና ቁጣ ያጎላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከፊቱ ከወጣው መብረቅ የእሳት ነበልባል ወደቀ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ከደማቅ ብርሃኑ የሚነድ እሳት ላከ" ወይም 2) "ከእርሱ ድምቀት መብረቅ ላከ"

እጅግ ከፍ ያለው ከፍ ባለ ድምጽ ተናገረ፡፡ ቀስቶችን ወረወረ

ዳዊት አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች እንደሚያደርግ ያህዌ ማድረጉን ይገልጻል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀስቶችን መረወረ… መብረቅ ወጣ

ዳዊት ከያህዌ አውሎ ነፋስ የሚወጣውን መብረቅ ወታደር ከሚጠቀምበት ቀስት ጋር ያነጻጽራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)