am_tn/2sa/22/10.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ሰማያትን ከፈተ… በሰማያት ጥቅጥቀው ያለ የዝናብ ደመና ነበረ

ዳዊት ያህዌ እርሱን ያዳነበትን መንገድ የገለጸው በአንድ ስፍራ እንደ ተከማቸ ሀይለኛ የዝናብ ደመና ከበዙ ጠላቶች አዳነኝ በማለት ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔርን ሃይል እና ቁጣውንም ያጎላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእግሮቹ ስር

ዳዊት እግአብሔር እንደ ሰው እግር እንዳለው አድርጎ ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በነፋስ ክንፎች ላይ ታየ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱ በነፋስ ክንፎች ላይ ታየ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የነፋስ ክንፎች

ይህ አገላለጽ ነፋስ ወፍ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጨለማን በዙሪያው ድንኳን አደረገ

እዚህ ስፍራ ያህዌ የፈጠረው ጨለማ የተነጻጸረው እርሱን ሙሉ ለሙሉ ከሸፈነ ድንኳን ጋር ነው፡፡ "እርሱ ራሱን በጨለማ ውስጥ ሰወረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)