am_tn/2sa/22/08.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም ምድር ተናወጠች… በቁጣው እሳት ነደደ

ዳዊት ከጠላቶቹ ለመዳን ለእርዳታ ላሰማው ጩኸት የያህዌ ምላሽ ይህ ነው፡፡ ዳዊት የምድርን መንቀጥቀጥ እና ከያህዌ እሳት የመምጣትን ምናብ የተጠቀመው የያሀድዌን አሰጨናቂ ቁጣ ለማጉላት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምድር ተናወጠች…ሰማያትም ተንቀጠቀጡ

ዳዊት ሁለቱን ጽንፎች የገለጸው በፍጥረት ውስጥ የሚገኘውን ሁሉ ለማካተት ነው፡፡ (ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ተቆጥቷል እና ተንቀጠቀጡ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእግዚአብሔር ቁጣ አናወጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከአፍንጫው…ከአፉ

ዳዊት ያህዌ እነዚህ የሰው አካሎች እንዳሉት አድርጎ ይናገራል፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ይመልከቱ)

በቁጣው ፍም ተቀጣጠለ

እዚህ ስፍራ የያህዌ ቁጣ ከሰል እንዲቀጣጠል እና እንዲነድ የሚያደርግ ከእሳት ጋር ተወዳድሯል፡፡ "ከአፉ የሚወጣው ነበልባል እሳት ያነዳል" ወይም "እንዲሁም እርሱ የሚነድ እሳት ከአፉ ይልካል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)