am_tn/2sa/22/07.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጭንቀቴ

"በታላቅ መከራዬ"

ከመቅደሱ ድምጼን ሰማ

ዳዊት የሚያመለክተው ያህዌ የሚኖርበትን ሰማያዊ መቅደስ ነው፡፡ ምድራዊው መቅድ ገና አልተገነባም ነበር፡፡

የእርዳታ ጥሪዬ ወደ ጆሮዎቹ ገባ

እዚህ ስፍራ "የእርሱ ጆሮዎች" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው ያህዌን እና ለእርዳታ የዳዊትን ጥሪ ማድመጡን ነው፡፡ "እርሱ ሊረዳኝ ልመናዬን ሰማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ጆሮዎች

ዳዊት ስለ ያህዌ ጆሮዎች እንዳሉት አድርጎ ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)