am_tn/2sa/22/05.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞት ማዕበል ከበበኝ፣ የጥፋት ጎርፍ ውሃ ዋጠኝ

ዳዊት ሊገድሉት የሚፈልጉትን ከፉ ሰዎች ሊውጠው ከደረሰ የጎርፍ ውሃ ጋር ያነጻጽራቸዋል፡፡ እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የዋሉትም ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የጥፋት ውሃ ጎርፍ

ይህ በመንገዱ ላይ ሚያገኘውን ሁሉ እየጠራረገ ሚያጠፋ በፍጥነት የሚወርድ የጎርፍ ውሃ ምስል ነው፡፡

የሲኦል ገመድ ተጠመጠበብኝ፤የሞት ወጥመድ ያዘኝ

ዳዊት ስለ ሞት እና ሲኦል የሚናገረው፣ አዳኝ እንስሳን እንደሚያጠምድ ሞት እና ሲኦል እርሱን ሊያጠምዱት የሚሞክሩ ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ነው፡፡ እነዚህ ሀረጋት ተመሳሳይ ትረጉም አላቸው ያገለገሉትም ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)