am_tn/2sa/22/03.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይቀጥላል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር አለቴ ነው… እርሱ ጋሻዬ ነው፣ የደህንነቴ ቀንድ፣ የእኔ መሸሸጊያ

እነዚህ ዘይቤዎች በሙሉ የእግዚአብሔር ጥንካሬ እና ሃይልና ምልክቶች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ህዝቡን የመጠበቅ እና የማዳን ችሎታ ያጎላሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሊወደስ የሚገባው ማን ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ውዳሴ ሊቀበል የሚገባው ማን ነው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጠላቶቼ እድናለሁ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ከጠላቶቼ ያድነኛል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)