am_tn/2sa/22/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ዳዊት ለያህዌ የሚያቀርበው መዝሙር ይጀምራል፡፡ የሚናገረውን ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ፣ ደግሞም ከሳኦል እጅ

ይህ በአጠቃላይ ከሁሉም ጠላቶች ወደ አንድ የዳዊት ጠላት፣ ወደ ንጉሥ ሳኦል የሚሄድ ነው፡፡

ከ…እጅ መዳን

ይህ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ "ከ… ሃይል መዳን" ማለት ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ የእኔ አለት ነው፣ የእኔ ምሽግ

ይህ ዘይቤ የሚያሳየው ከአንድ ክፍል ከ "አለት" አጠቃላይ ወደ ሆነ ነገር ማለትም ወደ "ምሽግ" የሚደረግ ሽግግርን ነው፡፡ ምሽግ ከብዙ ትልልቅ አለቶች የሚገነባ ነው፡፡ ይህ ማለት ያህዌ የእርሱን ህዝብ ከጉዳት ለመጠበቅ ጥንካሬ አለው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)