am_tn/2sa/21/18.md

1.4 KiB

ከዚህ በኋላ እንዲህ ሆነ

ይህ ሀረግ የታሪኩን አዲስ ክፈል ይጀምራል፡፡ ቋንቋችሁ ይህን ለማድረግ መንገድ ካለው፣ እዚህ ስፍራ ይህንን ለመጠቀም ትችላላችሁ፡፡

ጎብ

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ሴቦካይ… ሳፍ… የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን… ጎልያድ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ኩሳታዊ…ራፋማዊ… ቤተልሔማዊ… ጌታዊ

እነዚህ የሰዎች ቡድኖች/የወገኖች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ራፋይም

ይህ የህዝብ ወገን በግዙፋን ተዋጊዎቹ ይታወቅ ነበር፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ጦሮቻቸው እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ነበር

አንድ ሰው ሲሸምን የ"ሸማኔ መጠቅለያ" ተብሎ ከሚጠራ ትልቅ እንጨት ጋር በተያያዙ መቆንጠጫዎች መሃል ክሮቹን ያሳልፋል፡፡ ይህ ማለት የጎልያድ ጦር ከመደበኛው ጦር ትልቅ ነበር ማለት ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)