am_tn/2sa/20/23.md

1.8 KiB

አሁን

"አሁን" በዋናው ታሪክ ፍሰት ላይ አዲስ መስመር ያበጃል፡፡ ይህ አዲስ ክፍል ንጉሥ ዳዊትን ስለሚያገለግሉ ሰዎች የመረጃ ዳራ ይሰጣል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢዮአብ በ… ላይ ነበረ… የዮዳሄ ልጅ በናስያ በ…ላይ ነበረ… አዶኒራም በ… ላይ ነበረ

"በ…ላይ ነበረ" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው በአንድ ወገን ላይ ስልጣን ያለው መሆንን ነው፡፡ "ኢዮአብ በ… ላይ ስልጣን ነበረው፤ የዮዳሄ ልጅ በናስያ በ… ላይ ስልጣን ነበረው፤ አዶኒራም በ…ላይ ስልጣን ነበረው" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዮዳሄ… ኢዮሣፍጥ… አሒሉድ

የእነዚህን ወንዶች ስሞች በ 2 ሳሙሴል 18፡16-18 ላይ በተረጎሙት መሰረት ይተርጉሙት፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሊታውያን…ፈሊታውያን

እነዚህን የሰዎች/ቡድን ወገኖች ስሞች በ 2 ሳሙሴል 18፡16-18 ላይ በተረጎሙት መሰረት ይተርጉሙት፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የጉልበት ስራ እንዲሰሩ የተገደዱ ወንዶች

"ባሪያ ሰራተኞች"

አዶኒራም… ሱሳ…ዒራስ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢያዕራውያን

ይህ የሰዎች/ቡድን ወገን ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)