am_tn/2sa/20/20.md

3.2 KiB

ይህ ከእኔ ይራቅ፣ ከእኔ ይራቅ

ይህንን ሀረግ የደጋገመው ነገሩን በፍጹም የማያደርገው መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡ "በእውነት፣ በእውነት በፍጹም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ልውጣት ወይም ልደመስሳት

ይህ የሚያመለክተው ከተማይቱን ስለ መደምሰስ ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከተማችሁን ልውጣት ወይም ልደመስሳት ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

መዋጥ ወይም መደምሰስ

እነዚህ ሁለቱም ሀረጋት መደምሰስ ማለት ናቸው፡፡ በመጀመሪያው ሀረግ "መደምሰስ" የተገለጸው እንደ "መዋጥ" ተደርጎ ነው፡፡ እነዚህ በአንድነት ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ "ከተማይቱን ማፍረስ ወይም መደምሰስ" ወይም "መደምሰስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትረጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እጁን አነሳ

ይህ ማለት አንድን ሰው መቃወም እና መዋጋት ማለት ነው፡፡ "ተቃወመ" ወይም "በአመጸ መቃወም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ብቻ አሳልፈው እንዲሰጡ

ኢዮአብ የከተማይቱን ሰዎች ለእርሱ ሳቤዔን አሳልፈው እንዲሰጡት ጠየቅ፡፡ "ይህን ሰው ለእኛ አሳልፋችሁ ስጡን" ወይም "ይህንን ሰው ለእኛ ስጡን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከከተማይቱ እወጣለሁ

እዚህ ስፍራ "እኔ" የሚለው የሚያመለክተው ኢዮአብን እና ወታደሮቹን ጭምር ነው፡፡ "እኛ ከከተማይቱ እንወጣለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጭንቅላቱ ተቆርጦ ይወረወራል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጭንቅላቱን እንወረውራለን/ይጣልላችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም ሴቲቱ ወደ ህዝቡ ሁሉ በጥበብ ሄደች

ይህ ማለት ሴትየዋ በጥበብ አደረገች ደግሞም ለህዝቧ ማድረግ ያለባቸውን ተናገረች፡፡ "ከዚያም ጥበበኛዋ ሴት ለህዝቡ በሙሉ ተናገረች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ሰው ወደ የቤቱ

"እያንዳንዱ ሰው ወደ የራሱ ቤት ሄደ"