am_tn/2sa/20/17.md

2.4 KiB

የባሪያህን ቃል አድምጥ

ሴትየዋ ራስዋን "የአንተ አገልጋይ" በማለት ትገልጻለች፡፡ ይህ በስልጣን ከፍ ካለ ሰው ጋር በትህትና መነጋገሪያ መንገድ ነው፡፡

ያ ምክር ለነገሩ ፍጻሜ ይሰጣል

"ያ ምክር ችግሩን ይፈታል"

በእስራኤል ውስጥ እጅግ ሰላማዊ እና ትክክለኛ

ይህ ከተሞቹን ይገልጻል፡፡ "በእስራኤል እጅግ ሰላማዊ እና ትክክለኝ ከተሞች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

በእስራኤል እናት የሆነች ከተማ

ይህ በእስራኤል አገር የዚህን ከተማ ጠቀሜታ እንደ ተከበረች እናት አድርጎ ይገልጻል፡፡ "በእስራኤል የሚኖር ሁሉ እናቱን እንደሚያከብር የሚያከብራት ከተማ" ወይም "በጣም ጠቃሚ እና እስራኤል ሁሉ የሚያከብራት ከተማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን የያህዌን ርስት ለመዋጥ ትፈልጋለህ?

እዚህ ስፍራ ሴትየዋ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመችው ለኢዮአብ ማድረግ የማይገባቸውን እንዳያደርጉ ለመጠቆም ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ ርስቱ ያደረጋትን ከተማ መደምሰስ የለባችሁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መዋጥ

እዚህ ስፍራ ሴትየዋ ከተማይቱ የሚዋጥ ምግብ የሆነች ያህል ሰራዊቱ እንደሚደመስሳት ትገልጻለች፡፡ "መደምሰስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ርስት

እዚህ ስፍራ ከተማይቱ እንደ ያህዌ ርስት የተገለጸችው የያህዌ መሆኗን ለመጉላት ነው፡፡ "የያህዌ የሆነች ከተማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)