am_tn/2sa/20/06.md

2.5 KiB

አቢሳ

ይህ ሌላኛው የዳዊት ሰራዊት የጦር አዛዥ ነው፡፡ የዚህ ሰው ስም በ2 ሳሙኤል 2፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ ጉዳት ያደርስብናል

"የበለጠ ይጎዳናል"

የጌታችሁ አገልጋዮች፣ የእኔ ወታደሮች

"የእኔ ወታደሮች" የሚለው ሀረግ የትኞቹ "አገልጋዮች" እንደሆኑ ግልጽ ያደርጋል፡፡ ዳዊት ራሱን "የእናንተ ጌታ" በማለት ዝቅ ያለ ስልጣን ካለው ሰው ጋር ንግግር በሚደረግበት መደበኛ የአነጋጋር መንገድ ይገልጻል፡፡

ተከትለህ አባረው

"ከኋላ አሳደው"

የተመሸገ ከተማ ያገኛል

ይህ ማለት ሳቤዔ እና የእርሱ ወታደሮች ከዳዊት ሰራዊት ለመደበቅ ወደ እነዚህ ከተሞች ይገባሉ ማለት ነው፡፡ "እርሱ" የሚለው ቃል የሚወከወለው ሳቤዔን ሲሆን ነገር ግን እርሱን እና የእርሱን ወታደሮች ጭምር ያመለክታል፡፡ "እርሱ እና የእርሱ ሰዎች በተመሸገ ከተማ ራቸውን ይደብቃሉ" ወይም "እርሱ እና የእርሱ ሰዎች በተመሸጉ ከተሞች ይሸሸጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከእይታችን ውጭ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ሳቤዔ እና የእርሱ ሰዎች ሊደበቁ እንደሚችሉ እና የዳዊት ሰራዊት ሊይዛቸው እንደሚቸገር ትኩረት ለመስጠት ሰራዊቱን የሚገልጸው በእይታቸው ነው፡፡ "ከእኛ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከሊታውያን … ፈሊታውያን

እነዚህ ንጉሥ ዳዊትን ለመጠበቅ የረዱ የሰዎች ቡድን/ የወገን ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህ የወንድ ስሞች በ2 ሳሙኤል 8፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)