am_tn/2sa/18/19.md

1.5 KiB

አኪማአስ

ይህ የወንድ ስም በ2 ሳሙኤል 15፡27 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካሙን ወሬ ይዞ ወደ ንጉሡ ሮጠ

እዚህ ስፍራ አኪማአስ ስለ መሮጥ የሚናገረው ወደ ንጉሡ ሄዶ መለካሙን ወሬ/የምስራቹን እርሱ እንደተሸከመው አንድ ነገር ወይም አካል አድርጎ ነው፡፡ "መልካሙን ወሬ ለንጉሡ ለመናገር ሮጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የጠላቶቹ እጅ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው መቆጣጠርን/መያዝነን ነው፡፡ "ጠላቶቹን መቆጣጠር/መያዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ወሬውን ያመጣው/ወሬ ነጋሪው

"ወሬን የሚያደርሰው/የሚናገረው ሰው"

ምንም ወሬ አታደርስም

ይህ የሚያመለክተው ለንጉሡ ወሬ አለማምጣትን ነው፡፡ "ወሬውን ለንጉሡ አትናገርም/አታደርስም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)