am_tn/2sa/18/18.md

1.3 KiB

የንጉሥ ሸለቆ

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የስሜን መታሰቢያ የሚሸከመውን/ስሜን የሚያስቀጥለውን

አቤሴሎም "ስሜ/የእኔ ስም" የሚለውን ሀረግ የተጠቀመው ራሱን እና ቤተሰቡን ሀረግ ለማመልከቱ ነው፡፡ "ሰዎች እኔን የሚያስታውሱበትን፣ የቤተሰቤን ስም ለመሸከም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም መታሰቢያ ተብሎ ይጠራል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስለዚህም ሰዎች ከዚያን ጊዜ ቀን አንስቶ የአቤሴሎም መታሰቢያ ብለው ይጠሩታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ ዛሬ ቀን ድረስ

እዚህ ስፍራ ዛሬ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጻፈበትን ጊዜ ነው፡፡