am_tn/2sa/18/16.md

2.2 KiB

ኢዮአብ ሰራዊቱን ከልክሎ ነበርና መለከት ነፋ፣ እናም ሰራዊቱ እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ

ይህ ኢዮአብ መለከት በመንፋት ምን እንዳዘዘ ይገልጻል፡፡ "ከዚያም ኢዮአብ ሰራዊቱን ወደ ኋላ ለመመለስ መለከት ነፋ፣ እናም ሰራዊቱ እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ

እዚህ ስፍራ "እስራኤል" የሚያመለክተው የእስራኤላውያንን ሰራዊት ነው፡፡ "የእስራኤላውያንን ሰራዊት ከማሳደድ ተመለሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

አቤሴሎምን ወስደው ወረወሩት

"የአቤሴሎምን አካል/በድን ወስደው ወረወሩት"

በድኑን ከትልቅ የድንጋይ ክምር ስር ቀበሩ

በድኑን ጉድጓድ ውስጥ ከጨመሩ በኋላ በደንጋይ ክምር ሸፈኑት፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በድኑን በብዙ የድንጋይ ክምር ሸፈኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መላው እስራኤል በሚሸሽበት ጊዜ

እዚህ ስፍራ "መላው እስራኤል" የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን ወታደሮች ነው፡፡ "መሸሽ" የሚለው ቃል "ማምለጥ" ማለት ነው፡፡ "መላው የእስራኤል ወታደሮች በሚያመልጡበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)