am_tn/2sa/18/12.md

2.2 KiB

አንድ ሺህ የብር ሰቅል

"1,000 የብር ሰቅል፡፡" ይህ በዘመናዊ መለኪያ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "1,000 የብር ሳንቲም" ወይም "11 ኪሎ ግራም ብር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የገንዘብ መለኪያ እና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አላሳርፍም ነበር

"እጄን አላሳርፍም" የሚለው ቃል አልመታም ማለት ነው፡፡ "የንጉሡን ልጅ አልመታም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሊነካው አይገባም

እዚህ ስፍራ "መንካት" የሚለው የሚያመለክተው "መጉዳትን" ነው፡፡ "ማንም ሊጎዳ አይገባም" ወይም "አትጉዱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሀሰተኝነት

"ሀሰተኝነት" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ እንደዚሁም፣ ይህ የንጉሡን ትዕዛዝ አለመጠበቅን ያመለክታል፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስሀተት የሆነ ነገር መፈጸም" ወይም "ንጉሡን አለመታዘዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ምንም ነገር የለም

እዚህ ሰውየው የሚናገረው ንጉሡ እንዴት ከሞላ ጎደል ስለ ሁሉም ነገር እንደሚያውቅ ሲሆን ማናቸውም ነገር የሚለውም አካላዊ ቁስ ሆኖ ንጉሡ የዚይን ስፍራ እንደሚያውቅ አድርጎ ነው፡፡ "ንጉሡ የማያውቀው አንዳች ነገር የለም" ወይም "ንጉሡ ስለሚሆነው እያንዳንዱ ነገር ይሰማል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)