am_tn/2sa/18/09.md

2.4 KiB

አቤሴሎም ከዳዊት ጥቂት ወታደሮች ጋር በድንገት ተገናኘ

ይህ በጦርነቱ ወቅት ያጋጠመ ተዕይነት ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በጦርነቱ ወቅት አቤሴሎም ከጥቂት የዳዊት ወታደሮች ጋር ተገጣጠመ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጭንቅላቱ በግንድ ቅርንጫፎች መሃል ተይዞ ነበር

አቤሴሎም በዛፍ ቅርንጫፎች ሊያዝ የሚችል ረጅም ፀጉር ነበረው፡፡ "ፀጉሩ በዛፍ ቅርንጫፎች ተይዞ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መወዛወዝ

መሰቀል ወይም በቀስታ መወዛወዝ

እነሆ/ተመልከት

እዚህ ስፍራ ይህ ቃል ያገለገለው ቀጥሎ ለሚነገረው የአንባቢውን ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡ "ስማ/አድምጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ለምን መትተህ ወደ ምድር አታወርደውም ነበር?

የዚህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ትርጉም ሊገድለው ይገባ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "መትቶ ማውረድ" የሚለው ሀረግ መግደል ማለት ነው፡፡ "መትተህ ወደ ምድር ልታወርደው ይገባ ነበር!" ወይም "ወዲያውኑ ልትገድለው ይገባ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ))

አስር የብር ሰቅል

ይህ በዘመናዊ መለኪያ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አስር የብር ሳንቲም" ወይም "110 ግራም ብር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የገንዘብ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀበቶ

ይህ ለየት ያለ ቀበቶ ሲሆን ሰውየው ታላቅ ወታደር እና ሊከበር የሚገባው መሆኑን ለሰዎች የሚያሳይ ነው፡፡