am_tn/2sa/18/06.md

2.1 KiB

በእስራኤል ላይ ተነስቶ ወደ ገጠር/ ሜዳ መውጣት

ይህ ማለት ወጥተው በጦርነት ገጠሟቸው ማለት ነው፡፡ "ወደ ሜዳ/ገጠር ወጥተው ከእስራኤል ጋር ተዋጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእስራኤል ላይ

እዚህ ስፍራ "እስራኤል" የሚለው የሚያመለክተው ወታደሮቻቸውን እንጂ መላውን እስራኤላዊ አይደለም፡፡ "በእስራኤላውያን ወታደሮች ላይ"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያ ከዳዊት ወታደሮች አስቀድሞ የእስራኤል ሰራዊት ተሸነፈ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በዚያ የዳዊት ሰራዊት የእስራኤልን ሰራዊት አሸነፉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ እልቂት/መተራረድ

ብዙ ሰዎች በጭካኔ የሚገደሉበት ትዕይንት ሃያ ሺህ ወንዶች "20,000 ወንዶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በጫካው የተፈጁት/የተበሉት ወንዶች በለጡ

እዚህ ስፍራ "ጫካ/ዱር" የተገለጸው ህይወት እንዳለውና እርምጃ መውሰድ እንደሚችል ተደርጎ ነው፡፡ "ሰይፍ" የሚያመለክተው በሰይፍ የሚዋጉትን የዳዊት ወታደሮች ነው፡፡ "የዳዊት ወታደሮች በሰይፍ ከገደሏቸው ይልቅ በጫካ ውስጥ አደገኛ ነገሮች የገደሏቸው ሰዎች በዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)