am_tn/2sa/18/01.md

3.1 KiB

ዳዊት ከእርሱ ጋር የነበሩትን ወታደሮች ቀጠረ፣ ደግሞም ሾማቸው፡፡

ዳዊት ራሱ ህዝቡን ሁሉ አልቆጠረም፣ ህዝቡን የቆጠሩት ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡ ዳዊት ከእርሱ ጋር የነበሩትን የሚቆጠሩትን እና የሚሾማቸውን ወታደሮች አስተዳደረ/ለየ" ወይም "ዳዊት ከእርሱ ጋር የነበሩትን እና የሚሾማቸውን ወታደሮች አደራጀ፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሻለቆች እና የመቶ አለቆች

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እነዚህ ቁጥሮች መሪዎቹ የሚመሯቸውን ወታደሮች ትክክለኛ ቁጥር ይወክላሉ፡፡ "የ1,000 ወታደሮች እና የ100 ወታደሮች መሪዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው ወይም 2) "ሺህ" ወይም "መቶ" በሚል የተተረጎሙት ቃላት ቁርጥ ያለ ቁጥርን አይመክሉም፣ ነገር ግን ብዙ ወይም ትንሽ ቁጥር ያለውን የወታደር ክፍል ለመሰየም የዋለ ነው፡፡ "የትልቅ/ብዙ ወታደራዊ ክፍል አዛዥ እና አነስተኛ ቁጥር ያለው የወታደር ክፍል አዛዥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

አለቃ/አዛዥ

አለቃ በተወሰኑ የወታደር ስብስቦች/ቡድን ላይ ስልጣን ያለው ሰው

አንድ ሶስተኛ… ሌላ ሲሶ/ሶስተኛ

የሰራዊቱ አንድ ሶስተኛ… የሰራዊት ሌላ ሲሶ/ሶስተኛ፡፡ "ሲሶ/አንድ ሶስተኛ" እኩል የሆኑ ሶስት ክፍሎች አንድ ክፍል/አንድ እጅ፡፡ (ክፍልፋይ የሚለውን ይመልከቱ)

አቢሳ… ጽሩያ

እነዚህ የወንድ ስሞች በ2 ሳሙኤል 2፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢታይ

ይህ የወንድ ስም በ2 ሳሙኤል 15፡19 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ጌታዊ

ይህ ከፍልስጤም ከተማ ከጌት የሆነን ሰው ያመለክታል፡፡(ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም ራሴ በእርግጥ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ

ይህ ማለት ከእነርሱ ጋር ለጦርነት አብሯቸው ይመጣል ማለት ነው፡፡ ይህ ይበልጥ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ ራሴ ከእናንተ ጋር አብሬ ለጦርነት እወጣለሁ" ወይም "እኔ በግል ወደ ጦርነት አብሬያችሁ እሄዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)