am_tn/2sa/17/21.md

1.7 KiB

እንዲህም ሆነ

"እንዲህ ሆነ፡፡"ይህ ሀረግ በታሪኩ ፍሰት ቀጣዩን ትዕይንት ያመለክታል፡፡ (አዲስ ትዕይንትን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

በፍጥነት ውሃውን ተሻገሩ

እዚህ ስፍራ "ውሃው" የሚለው የሚያመለክተው የዮርዳኖስን ወንዝ ነው፡፡ "ባህሩን በፍጥነት ተሻገሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን እና ያንን ምክር ሰጠ

"ይህንን እና ያንን" የሚለው ፈሊጥ በአንባቢው ቀደም ሲል በሚታወቅ መረጃ ስፍራ የዋለ ነው፡፡ እዚህ ቦታ ይህ የሚያመለክተው አኪጦፌል አቤሴሎምን በ 2 ሳሙኤል 17፡1-3 የመከረውን ነው፡፡ ይህ መረጃ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አሁን አንተን ለማጥቃት አቤሴሎም እርሱን ከሰራዊት ጋር እንዲልክ መክሮታል" (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እስከ ጠዋት የዮርዳኖስን ወንዝ ያልተሻገረ ማንም አልነበረም

ይህ አሉታዊ ዐረፍተ ነገር የዋለው ሁሉም ወንዙን ማቋረጣቸውን ለማጉላት ነው፡፡ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በማለዳ እያንዳንዳቸው ዮርዳኖስን አቋረጡ" (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)