am_tn/2sa/17/15.md

1.5 KiB

ሳዶቅ… አብያታር

እነዚህን የወንድ ስሞች በ 2 ሳሙኤል 15፡24-25 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህና ይህን በመሰለ መንገድ

ይህ ሀረግ፣ ማለትም "እንደዚህ አይነት" የሚለው የሚያመለክተው አኬጦፌል ቀደም ሲል በ2 ሳሙኤል 17፡1-3 ላይ አቤሴሎምን የመከረውን ምክር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የመሻገሪያ ዳርቻ

መሻገሪያ ሰዎች በእግራቸው ሊያቋርጡት የሚችሉት የወንዙ ጥልቀት የሌለው የውሃ ክፍል ነው፡፡ ዳርቻ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሁለትም ጎኖች የሚገኝ መሬት ነው

በማናቸውም ብልሃት/መንገድ

ይህ ማለት አንድ ነገር ስለ ማድረግ እርግጠኛ መሆን ነው፡፡ "ለማድረግ እርግጠኛ መሆን" ወይም "ለማድረግህ እርግጠኛ ሁን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሡ ይዋጣል

እዚህ ንጉሡ እና ህዝቡ መገደላቸው የተገለጸው በጠላቶቻቸው "እንደሚዋጡ" ተደርጎ ነው፡፡ "ንጉሡ ይገደላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)