am_tn/2sa/17/13.md

2.6 KiB

ከዚይም መላው እስራኤል

ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን ወታደሮች እንጂ መላውን እስራኤላዊ አይደለም፡፡ "ከዚያም መላው ወታደራችን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደዚያች ከተማ ገመድ እናመጣለን ደግሞም ወደ ባህር ውስጥ እናሰጥማታለን

ይህ ማለት ወታደሮች የከተማይቱ ቅጥር ያፈርሳሉ፤ ፍርስራሹንም ጎትተው ወደ ባህር ይጥላሉ፡፡ "ከተማይቱን እንደመስሳለን ደግሞም ድንጋዬቹን በገመድ ስበን ወደ ባህር እንጨምራለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ትናንሽ ድንጋይ እንኳን በዚያ እስከማይገኝ ድረስ

ይህ ከተማይቱን ምን ያህል ሙሉ ለሙሉ እንደሚያጠፏት ለመግለጽ የቀረበ ግነት ነው፡፡ ከከተማይቱ እያንዳንዲቱን ድንጋይ ጠርገው አያስወግዱም፡፡ "ከተማይቱ ሙሉ ለሙሉ እስክትጠፋ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና ጥቅል አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

አርካዊው ኩሲ

ይህ የወንድ ስም በ 2 ሳሙኤል 15፡32 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ አርካዊ የህዝብ/ሰዎች የቡድን ስም ነው፡፡

አኪጦፌል

ይህ የወንድ ስም በ 2 ሳሙኤል 15፡12 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

የአኪጦፌልን መልካም ምክር መቃወም/መጣል

"አለመቀበል/መጣል" የሚለቀው ቃል "ተቃወመ/ጣለ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእስራኤል ወንዶች የአኪጦፌልን መልካም ምክር ላለመቀበል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመለከቱ)

በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት

በአንድ ነገር ላይ አንደን ነገር ለ "ማምጣት" ማለት በእነርሱ ላይ እንዲሆን ማለት ነው፡፡ "ጥፋት በአቤሴሎም ላይ እንዲመጣ ምክንያት መሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)