am_tn/2sa/17/08.md

3.0 KiB

እነርሱ ልጇ እንደተነጠቁባት ድብ ናቸው

እዚህ ስፍራ የወታደሮቹ ቁጣ የተነጻጸረው ግልገሎቿ ከእርሷ ከተወሰዱባት አንዲት እናት ድብ ጋር ነው፡፡ "ግልገሎቿ እንደ ተወሰዱባት እናት ድብ ተቆጥተዋል፡፡" ወይም "እነርሱ በጣም ተቆጥተዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድብ

በአራት እግሩ የሚራመድ ስል መንጋጋ እና ጥርሶች ያለው ግዙፍ ፀጉራም እንስሳ

የጦር ሰው ነው

ይህ ማለት በብዙ ጦርሜዳ የተዋጋ እና የጦርነት መንገዶችን በሚገባ የሚያውቅ፡፡ "በብዙ ጦርሜዳ የተዋጋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እይ/እነሆ

ይህ ቃል አድማጩ ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡ "ስማ/አድምጥ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡

ጉድጓድ

የተቆፈረ ጥልቅ መሬት

ወይም በሌላ አንድ ስፍራ

ይህ እርሱ ሊደበቅበት የሚችልበት ሌላ ስፍራ ነው፡፡ "ወይም በሌላ ስፍራ ተደብቋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንተ ሰዎች ጥቂቶች በተገደሉ ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእርሱ ወታደሮች ከአንተ ሰዎች ጥቂቶችን በገደሉ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አቤሴሎምን በተከተሉ ወታደሮች መሃል እርድ/እልቂት ተፈጸመ

"ማረድ/ማለቀ" የሚለው ስም ብዙ ሰዎች በጭካኔ የተገደሉበት ትዕይንት ማለት ነው፡፡ ይህ እንደ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አቤሴሎምን ከተከተሉት ወታደሮች ብዙዎቹ ታረደዋል" ወይም "የጠላት ወታደሮች አቤሴሎምን ከተከተሉት ወታደሮች ብዙዎችን ገድለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ልቦቻቸው እንደ አንበሳ ልብ የሆነ

እዚህ ስፍራ ወታደሮች የተገለጹት የእነርሱ "ልቦች" በሚለው ነው፡፡ እንደዚሁም፣ ጠንካራ ጀግንነታቸው ከአንበሳ ብርታት ጋር ነው፡፡ "እንደ አንበሶች ጀግና የሆኑ" ወይም "በጣም ጀግና የሆኑ" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)