am_tn/2sa/16/22.md

2.4 KiB

ዘረጉ

"አበጁ"

እስራኤል ሁሉ እየተመለከተ

ይህ ማለት ህዝቡ ደንኳኑን እና አቤሴሎም ከሴቶቹ ጋር ወደ ደንኳኑ ውስጥ ሲገባ እና ሲወጣ ይመለከት ነበር ማለት ነው፡፡ "መላው እስራኤል" የሚለው ሀረግ በቤተ መንግሥቱ አቅራቢያ የሚገኙ ሰዎች ብቻ ይህን ሊመለከቱ እንደሚችሉ የሚገልጽ አጠቃላይ አስተያየት ነው፡፡ "ወደ ድንኳን ሲገባ እስራኤላውያን ሊመለከቱ የሚችሉበት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚለውን ይመልከቱ)

የአኪጦፌል ምክር… አንድ ሰው …እንደ መስማት ማለት ነበር

እዚህ ስፍራ ጸሐፊው ሰዎች ምን ያህል የአኪጦፌልን ምክር በቀጥታ ከእግዚአብሔር መስማትን ያህል እንሚያምኑበት ያነጻጽራል፡፡ "በነዚያ ወቅት ሰዎች የአኪጦፌልን ምክር ከ… እንደ ተጠየቀ/እንደ መጣ አድርገው ያምኑበት ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በቀጥታ እንደ ሰማ

እዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር አፍ የሚለው የሚወክለው ራሱን እግዚአብሔርን እና የእርሱን ቃል ነው፡፡ "እግዚአብሔር በራሱ አፍ የተናገረውን ያህል" ወይም "አንድ ሰው በራሱ በእግዘአብሔር ሲነገር የሰማውን ያህል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ተጠቃሽ ተውላጠ ስም የሚሉትን ይመልከቱ)

የአኪጦፌል ምክር በሙሉ በዳዊት እና በአቤሴሎም በሁለቱም… ይታይ/ይቆጠር ነበረው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ዳዊት እና አቤሴሎም ሁለቱም የአኤጦፌልን ምክር… ይመለከቱ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ይታይ/ይቆጠር ነበር

"ይታሰብ ነበር"