am_tn/2sa/16/07.md

2.2 KiB

ክፉ/ተንኮለኛ

ክፉ፣ ወንጀለኛ ወይም ህግ የማያከብር ሰው

የደም ሰው

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው የሚያመለክተው እርሱ ተጠያቂ ለሆነባቸው በጦርነት ለተገደሉ ሰዎች ሁሉ ነው፡፡ "ነብሰ ገዳይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ የስራህን እየከፈለህ ነው

ያህዌ እነርሱን በመቅጣት እየከፈላቸው ነው፡፡ ይህ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ ቀጥቶሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በሳኦል ቤት ውስጥ ላፈሰስከው ደም

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው የሚያመለክተው ከሳኦል ቤት የተገደሉ ሰዎችን ነው፡፡ ንጉሡ ለእነርሱ መሞት ተጠያቂ ነው፡፡ "ብዙዎቹን የሳኦል ቤተሰቦች በመግደል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በማን ስፍራ/የማንን ስፍራ ይዘህ ስትገዛ ኖርክ

ዳዊት ንጉሥ ሆኖ የገዛው ሳኦል አስቀድሞ ይገዛቸው የነበሩትን እነዚያኑ ህዝቦች ነው፡፡ "ንጉሥ ሆነህ የገዛኸው በማን ስፍራ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በአቤሴሎም እጅ ውስጥ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚያመለክተው በቁጥጥር ስር ማድረግን ነው፡፡ "በአቤሴሎም ቁጥጥር ስር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)